Sunday, December 29, 2013

ከፖሊሲ አልቦነት የመነጨ የወንበዴዎች ወንበዴ መግለጫየኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ሰሞኑን አንድ መግለጫ አውጥቶ ነበር- "ሰላማዊ ተቃውሞን መዝጋትና የዜጎችን ህገመንግስታዊ መብቶች ማፈን በአስቸኳይ ሊቆም ይገባዋል" በሚል ርዕስ።


ምን አይነት አማራጭ ፖሊሲዎች እንዳሉት በውል የማይታወቀውና እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ አቋሞችና ፖሊሲዎች ያሏቸው ፓርቲዎች ያካተተውን መድረክ የኢትዮጵያ ሕዝብ "ይህ ነው" ብሎ ለየቶ አያውቀውም፡፡ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ተለይቶ በህዝብ እንዲታወቅ የሚያደርጉት አቋሞቹና ፖሊሲዎቹ ናቸው። ይሁን እንጂ መድረክ የተሰኘውን ፓርቲ "ይህ ነው" ብሎ ለመለየት የሚያስችል ግልፅ ፖሊሲና አቋም ስለሌለው እስካሁን ሕዝቡ ለይቶ ሊያውቀው ያልቻለው፡፡ የሚያውቁት አሉ ቢባል እንኳን እውቀታቸው በአቋምና ፖሊሲዎቹ ሳይሆን፣ ማንኛውንም ፅንፈኛ ተቃዋሚ በልሳንነት ለማገለገል ታጥቀው የቆሙ አንዳንድ የግል ፕሬሶች በሚያወጡት "መድረክ ተፈለጠ፣ ተቆረጠ፣ ምንትስ ቅብጥርስ ሆነ . . ." በሚል የዜና ርዕስ ላይ ከሰፈረ "መድረክ" የተሰኘ ስያሜ ያለፈ አይደለም፡፡

ለአንድ የፖለቲካ ፓርቲ መቃወም በራሱ መድረሻ አይደለም፡፡ መድረሻው ተቃውሞን ተከትሎ ግልፅ አማራጮችን ምክንያታዊ የሆኑ አቋሞችን ማቅረብ ነው፡፡ መድረክ ይህን ሲያደርግ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም። በውስጡ ያቀፋቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያየ መነሻና ግብ ያላቸው በመሆናቸው ይህን ማድረግ ይከብደዋል። የፓርቲው አመራሮች ገዢው ፓርቲና መንግስት ላይ ባላቸው ጭፍን ጥላቻ የሚመሩ፣ ይህን ጥላቻቸውንም ለማስታገስ በማለም ወደፖለቲካው ዓለም ዘው ብለው የገቡ በመሆናቸው አንድም ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚበጅ ራዕይና አቋም መቋጠር አልቻሉም፡፡ በዚህ ላይ ሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ ለፖለቲካ ፍጆታ ይውላል ብለው ያሰቡት ሁነት ሲገኝ ብቻ የሚሰባሰቡ የትርፍ ሰአት ፖለቲከኞች በመሆናቸው ግዜ ወስደው ረብ ያለው፣ ለአገር የሚጠቅም ሃሳብ ማመንጨትና መተግበር የሚችሉ አይደሉም።

ወደ መግለጫቸው እንመለስ፤ እንደተለመደው የሰሞኑ የመድረክ መግለጫ ከዚሁ አመራሮቹን እግር ከወርች ጠፍንጎ በያዘ መሰረተ ቢስ ጥላቻ የተቃኘ ነው። መድረክ መግለጫውን ለማውጣት መነሻ ሆነኝ ያለው በህገወጥ መንገድ ወደሳዑዲ አረቢያ ገብተው የነበሩ ኢትዮጵያውያንን ከአገር ከማስወጣት ጋር በተያያዘ የተፈፀመው ተገቢ ያልሆነ እርምጃ ነው። መድረክ "ይህን የሳዑዲ አረቢያ መንግስት እርምጃ ተቃውሜ ሰልፍ ለመውጣት ጠይቄ ተከለከልኩ" ባይ ነው።

እርግጥ ነው ፓርቲው ህዳር ወር አጋማሽ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ጠይቆ ሰልፉ እውቅና ሳይሰጠው ቀርቷል። ይሀ የሆነበት አቢይ ምክንያት ጉዳዩ በሚመለከተው የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ባለስልጣን በግልፅ ተነግሮታል። ሰልፉ የተከለከለው ሁላችንም እንደምናውቀው አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎቸ የባቡር መስመርና ሌሎች የኮንስትራክሽን ስራዎች በመከናወናቸወ የትራፊክ መጨናነቅ በመፈጠሩ እንዲሁም በዚያ ሰሞን አዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን በማስተናገድ ላይ በመሆኗ የፀጥታ አስከባሪ የፖሊሰ ኃይል እጥረት በመኖሩ . . . መሆኑ በግልፅ ቋንቋ ተነግሮታል።

በአሁኑ ግዜ በተለይ መስቀል አደባባይ አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ በማይቻልበት ሁኔታ የትራፊክ መጨናነቅ መኖሩን ሁሉም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ያውቀዋል፡፡ በየአመቱ መነሻና መድረሻውን እዚሁ አካባቢ በማደረግ ይካሄድ የነበረው ታላቁ ሩጫ በጃል ሜዳ አካባቢ እንዲካሄድ የተወሰነውም በዚሁ ምክንያት መሆኑ ግልፅ ነው። እኔ እንደሚገባኝ የፖለቲካ ፓርቲን የሚያህል ህጋዊ ዕውቅና ኖሮት የሚንቀሳቀስ ተቋም በአንድ ጉዳይ ላይ ያለውን ድጋፍ ወይም ተቃውሞ ለመግለፅ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣት ብቸኛውና በማንኛውም ሁናታ የተሻለ አማራጭ አይደለም፡፡ እናም መድረክ የሳዑዲአረቢያ መንግስት በአገሩ በነበሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ የፈፀመውን ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ለመቃወም የግድ ሰልፍ መውጣት አይኖርበትም፡፡ "ከአንጀት ካለቀሱ. . ." እንዲሉ ፓረቲው ከምር ድርጊቱን ተቃውሞ ከነበረ የተሻለ ተፅዕኖ መፍጠር የሚያስችሉ በርካታ መንገዶች ነበሩለት፡፡ ለምሳሌ በጉዳዩ ላይ ጠንከር ያለ የአቋም መግለጫ አውጥቶ፣ የዓለም መንግስታትና ዓለም አቀፍ ተቋማት እውነታውን እንዲያውቁት፣ እንዲያወግዙትና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን እርምጃዎች እንዲወስዱ ማሳሰብ ይችል ነበር፡፡ ይህን ማደረግ አዲስ አበባ አደባባዮች ላይ ወጥቶ መፈክር በማሰማት ከሚደረግ ሰልፍ የበለጠ ተፅእኖ ፈጣሪ መሆኑ መታሰብ አለበት። 3


ወትሮ ተፈለጥኩ፣ ተቆረጥኩ ብሎ ለየኤምባሲው፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ነን ለሚሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች . . . ደብዳቤ በመላክና መግለጫ በማቀበል የሚታወቀው መድረክ በሳዑዲ አረቢያ በደል የተፈፀመባቸው ኢተዮጵያውያን ጉዳይ ላይ ይህን እንዳያደርግ ማን/ምን ወገቡን ያዘው?

ፓርቲው፣ መድረክ ተሚባለው ማለት ነው፣ ይህን ማድረግ ያልመረጠበት በርካታ ምክንያቶች አሉት። አንዱ ምክንያት የኢፌዲሪ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ጠንካራ አቋም ይዞ የዜጎቹን መብት ለማስከበር ተገቢና በአቅሙ ውስጥ ያሉትን እርምጃዎች በሙሉ ስለወሰደ በሳዑዲ አረቢያ መንግስት ላይ የሚወጡ የተቃውሞ መግለጫዎች መንግስትን መደገፍ ሆኖ የሚሰማው ከመሆኑ የመነጨ ነው። መድረክና አመራሮቹ በጭፍን ጥላቻ የሚነዱ በመሆናቸው በመንግስት የሚከናወኑ በጎ እርምጃዎች በሙሉ ይሸክኳቸዋል፡፡ ሌላው ምክንያት መድረክ በራሱ ችግር በምርጫ የህዝብ ድምፅ አግኝቶ በውክልና የመንግስት ስልጣን መረከብ እንደማይችል ከመገንዘቡ የመነጨ ነው። የመድረክ መሰረታዊ ውስጣዊ ችግር የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታን ያገናዘበ፣ በህዝብ ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችል ግልፅ ፖሊሲና አቋም ከማጣቱ የሚመነጭ ነው፡፡ ኢህአዴግ ላይ ቅሬታ ያላቸውና ችግሮቹን የሚናገሩ ቅን ዜጎችም ይህን የመድረክ ችግር በአግባቡ ተገንዝበውታል።

ከአስር አመት በፊት የአዲስ አበባና የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤቶች ፕሬዝዳንት የነበሩት፣ በምርጫ 97 ወቅትም የተቃዋሚውን ጎራ ተቀላቅለው የነበሩት፣ በአሁኑ ወቅት የኢኒሼቲቭ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት ታዋቂው ነጋዴ አቶ ክቡር ገና ጥቅምት 14፣ 2006 ዓ/ም በአሜሪካ ድምፅ የአማርኛ ፕሮግራም ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ወቅት ከጋዜጠኛው "የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ከተቃዋሚ ፓርቲዎችና ከኢህአዴግ አኳያ ሲገመሙት ምን ይመስላል?" የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ሲመልሱ እንደሚከተለው ነበር ያሉት፤

እንደሚታወቀው አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሚና እየጨመረ የሚመጣው ወደ ምርጫ አካባቢ ነው፡፡ ግን በአጠቃላይ ስመለከተው የተለየ ፕሮግራምና ያ የተለየ ፕሮግራም ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ሁኔታ ወደ ተሻለ ሁኔታ ለማምጣት የሚያስችል ፕሮግራም ስለመሆኑ እስካሁን በተቃዋሚዎች በኩል ለሕዝብ ቀርቦ አያውቅም፡፡ ተቃዋሚው ሃይል መንግስትን ሲቃወም እንጂ፣ ተቃውሞ የራሱ ፕሮግራም በምን መልኩ የተሻለ መሆኑን ተናግሮ አሳምኖ በተለየ የኢትዮጵያን ሕዝብ ፍላጎት ሊያረጋግጥ የሚችለው ‘ይሄኛው ነው’ የሚለው እስካሁን 

በግልፅ አልታየም፡፡ ስለዚህ ‘የተሻለ ሁኔታ ላይ ያለው አሁንም ኢህአዴግ ነው’ ብዬ ነው የምገምተው።

ያለው ተጨባጭ እውነታ የኸው ነው!!

እንግዲህ መድረክ በህዝብ ሊመረጥና የስልጣን ውክልና ሊያስገኝ የሚያስችል አማራጭ ስለሌለው፣ መንግስትን ከስልጣን ሊያስወግድልኝ ይችላል ብሎ የገመተውን ማንኛውንም አጀንዳ ለመጠቀም ቆርጦ መነሳቱን የሚያመለክቱ አዝማሚያዎችም ይታያሉ። መንግስት ላይ የከረረ ተቃውሞ ያለው ማንኛውም ወገን ላይ፣ የተቃውሞ መነሻ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ለመለጠፍ ከመሞከር ወደኋላ የማይል መሆኑ አንዱ አመላካች ነው። የመድረክ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና በአክራሪዎችና ግልፅ በወጣ የአሸባሪዎች እንቅስቃሴና ድርጊት ላይ የሚያሰሙት አቋም ለርእሰ ጉዳያችን ከበቂ በላይ አስረጂ ሆኖ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

መድረክ የአደባባይ የተቃውሞ ሰልፎች፣ ከሶስት አመታት ቀደም ብሎ በአረብ አገራት አብዮቶች ላይ አንደታየው ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የከተማ ነውጥ ሊፈጠር ይችላል የሚል ግምት ያለው ይመስላል። በዚህ መነሻነት እንደ ፖለቲካ ፓርቲ በርካታ ተፅእኖ ማሳደር ለሚችሉ ሰላማዊ የተቃውሞ አማራጮች ዋጋ ሳይሰጥ፣ አመቺ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥም ቢሆን የተቃውሞ ሰልፍ ካልጠራሁ ብሎ መሟገቱን መርጧል፡፡ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በሃገሩ ይኖሩ በነበሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን ተገቢ ያልሆነ እርምጃ ተፅእኖ ሊፈጥር በሚችል መንገድ መቃወም፣ ለዜጎቻችንም መብት መከበርና ዘላቂ ኑሮ ጠቃሚ የሆኑ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ጫና ማሳደር የሚቻልበትን እድል መሞከሩን እርግፍ አድርጎ ትቶ ግዳዩን ለራሱ የፖለቲካ ትርፍ ማግበስበሻነት ለማዋል ሲፈጨረጨር ነው የሚታየው፡፡

መድረክ ሰላማዊ ሰልፍ ተከለከልኩ የሚለውን መነሻ በማደረግ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ ካነሳቸው ሃሳቦች መሃከል እንዲሁም አመራሮቹ መግለጫውን አስታከው ካሳወቁዋቸው አቋሞች መሃከል ጥቂቶቹን እንመልከት፡፡ በመግለጫው ርዕስ ላይ "ሰላማዊ ተቃውሞን መዝጋት . . ." በሚል ከተጠቀሰው ሃሳብ እንጀምር፤

በመድበለ ፓርቲ ስርዓት የተለያየ፣ እርስ በርስ የሚቃረን አመለካከትና አቋም ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ፓረቲዎቹ አንዱ የሌላውን አመለካከት አክብሮ፣ የራሱ 

አመለካከት፣ አቋምና ፖሊሲ የህዝብን ይሁንታ እንዲያገኝ ፣ በህዝብ ውክልና ለስልጣን ውክልና እንዲበቃ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ ሰላማዊ ያልሆኑ የሁከት መንገዶችን ፣ የጥላቻ ፓለቲካ ዘመቻዎችን በማካሄድ መጠላለፍ ውስጥ መግባት አይችሉም። ይህ ከዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ባሕል፣ ከሕግም ውጭ ነው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ያህል የተለያየ አቋም ቢኖራቸው በወሳኝ የጋራ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተግባብተው መስራት ይጠበቅባቸዋል። የአገራቸውን ዘላቂ ሕልውናና የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ የህዝብ የስልጣን ውክልና የሚረጋገጥበትን ሰላማዊው የምርጫ ሂደትና አጠቃላይ ሰላማዊ የፖለቲካ ምህዳርን በመጠበቅ ዴሞክራሲን ማጎልበትና መሰል አገራዊ ጉዳዮች ላይ ነው መግባባት የሚጠበቅባቸው።

ከአገራዊ ጉዳዮች መሃከል ሁሉንም ፓርቲዎች በእኩል ደረጃ የመያሳተፈውና የሕዝብ የስለጣን ምንጭና ባለቤትነት የሚረጋገጥበት ምርጫ ቀዳሚው ነው። ከሰላማዊ ምርጫ ውጭ የህዝብ የስልጣን ባለቤትነት የሚረጋገጥበት ዴሞክራሲያዊ ስርአት መገንባት የማይታሰብ ነው። በዚህ የዴሞክራሲ መሰረት በሆነ የምርጫ ተሳተፎ ላይ ፓርቲዎች ለህግና ለፖለቲካ ስነ ምግባር ተገዢ ሆነው መገኘት ይጠበቅባቸዋል። በዚህ መሰረት በኢትዮጵያ በ2002 ዓ/ም (4ኛው ዙር ምርጫ ከመካሄዱ አስር ወር ያህል ቀደም ብሎ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሁሉም በምርጫ ተሳታፊ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚገዙበት የምርጫ ሥነ ምግባር ደንብ ረቂቅ አዘጋጅቶ ፓርቲዎቹ እንዲወያዩበት ጋብዞ ነበር። ይህ የውይይት መድረክ የተሳለጠ ሰለማዊ የፖለቲካ ትግል እንዲካሄድ ሁኔታዎችን የሚያመቻች

Source: Aigaforum

No comments:

“ምስ ህዝቢ ምርኻብ ፍርቂ መንገዲ ዓወት‘ዩ”

Tigrai Online “... ገፅ መራሕትና ካብ ዘይንርኢ፣ ንመራሕትና ካብ እንናፍቖም ዳርጋ 20 ዓመታት ኣቚፂርና፡፡  ናብ ከባቢና ሓንቲ መኪና እንተመፂኣ ኣንታ መን‘ኮን ሒዛ መፂኣ ? እናበልና ብሃንቀውታ ነመዓዱ፡፡...